አይ ቢ ዲ ን ለመመርመር ምን ያስፈልጋል?
ዶክተርዎ አልሰሬቲቭ ኮላይተስ ወይም ክሮንስ በሽታ እንዳለብዎ ከጠረጠረ አንዳንድ ምርመራዎችን ወስደው በሽታው ምን እንደሆነ ተመርምረው ማረጋገጥ ይኖርበዎታል። የአይ ቢ ዲ በሽታ በአንድ ምርመራ ብቻ አይታወቅም ። በሽታውን ለማረጋገጥ ዶክተርዎ የተለያየዩ ምርመራዎችን ማድረግ ያስፈልገዋል።
ደም እና ሰገራ ምርመራ
የደም ምርመራዎች በሰውነትዎ የሆነ ቦታ ውስጥ ቁስል (የጨመረ ሲ አር ፒ ወይም ኢ ኤስ አር) እና የደም ማነስ እንዳለብዎ እና እንደሌለብዎ (ዝቅተኛ ሄሞግሎቢን) ሊያሳዩ ይችላሉ። አይ ቢ ዲ ያለበት ህመምተኛ ሁለቱ በጣም የተለመዱ ግኝቶች ናቸው። እንዲሁም እንደ ጉበት እና ኩላሊት ያሉ የሰውነት አካል ክፍሎች በትክክል እየሰሩ መሆናቸውን እና ሌሎች የማዕድናት ወይም የቫይታሚኖች እጥረት ካለብዎ ሊያሳዩ ይችላሉ።
የደም መፍሰስ ወይም የቁስለት ምልክቶች (ካልፕሮቴክቲን) እና ተቅማጥዎ በኢንፌክሽን ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ለማወቅ ሰገራዎ ሊመረመር ይችላል።
ኢንዶስኮፒ
ኢንዶስኮፒ ለዚህ የምርመራ አይነት ጠቅላላ ስሙ ሲሆን ባለሙያ ዶክተር (ኢንዶስኮፒስት) ኢንዶስኮፒን በመጠቀም የምግብ መፍጫ ስርዓት ውስጥ በቀጥታ እንዲመለከት ይረዳዋል። አይ ቢ ዲ መኖሩ ከተጠረጠረ፣ ወደ ህክምና ወይም የቀዶ ጥገና ጋስትሮኢንተሮሎጂስት በመሄድ የኢንዶስኮፒ ምርመራ እንዲያደረጉ ይመከራል።
በኤንዶስኮፒ ውስጥ አንድ ዶክተር ወይም ስፔሻሊስት ኢንዶስኮፒስት የምግብ መፍጫ ስርዓትን ለመመርመር ረጅም ቀጭን፣ ብዙን ግዜ የሚተጣጠፍ፣ ጫፉ ላይ ካሜራ ያለው – ኢንዶስኮፕ ይጠቀማል። በሚመረመረው የአንጀት ክፍል መሰረት የተለያየ ስሞች ያሏቸው ብዙ አይነት የተለያዩ ኢንዶስኮፒዎች አሉ።
የላይኛው የጂ አይ ኢንዶስኮፒ ወይም ጋስትሮስኮፒ፣ የላይኛው የምግብ መፍጫ ሥርዓት ክፍልዎን ማለትም እንደ ኢሶፋገስ እና ሆድን የመሳሰሉትን ለማየት ይጠቅማል። የሚከተተው በአፍ ውስጥ ነው።
ኮሎኖስኮፒ ወይም ሲግሞይዶስኮፒ ትልቁን አንጀት ለማየት ይጠቅማል። ፊንጢጣን እና ትልቁ አንጀትን ለመመርመር ሲግሞይዶስኮፕ (አጭር ኢንዶስኮፕ) ወይም ኮሎኖስኮፕ (ረዘም ያለ እና የሚተጣጠፍ ኢንዶስኮፕ) በፊንጢጣ (የኋላ ማለፊያ) በኩል ይከተታል።
ኢንዶስኮፒ ማመም የለበትም ነገር ግን ደስ የማይል ስሜት ይፈጥራል፣ ስለዚህ ዘና ለማለት እንዲረዳዎ ማስታገሻ ይሰጥ ይሆናል። ባዮፕሲ (ትንሽ የቲሹ ናሙናዎች) ብዙውን ጊዜ በ ኢንዶስኮፒ ወቅት ይወሰዳሉ። እነዚህም የ አይ ቢ ዲ በሽታን ለማረጋገጥ በማይክሮስኮፕ ሊመረመሩ ይችላሉ።
የእንክብል ወይም ካፕሱል ኢንዶስኮፒ በምግብ መፍጫ ስርዓት በኩል የምታልፍ፣ የአንጀት የውስጠኛውን ክፍል ፎቶ የምታነሳ፣ ልዩ የሆነች በጣም ጥንጥ የምትዋጥ ካሜራ (ትንሽዬ ወይን የምታክል) አይነት ኢንዶስኮፒ ናት። የእነዚህ ፎቶዎች ወገብ ላይ ተደርገው መረጃ ወደሚቀዳ ይተላለፋሉ። ካፕሱሉ በመፀዳጃ ወቅት ከሰውነት የሚወጣ እና የሚወገድ ነው። ሁሉም ማዕከሎች የካፕሱል ኢንዶስኮፒን አያሰጡም። ለሁሉም ሰው ደግሞ ተስማሚ ላይሆን ይችላል።
የሆድ ራጅ እና ሲቲ ስካን
አይ ቢ ዲ ውስጥ የምንጠቀማቸው ብዙ የተለያዩ ራጆች አሉ። ቀላል የሆድ ራጅ ለድንገተኛ ጊዜ ወይም መጀመሪያ ላይ አይ ቢ ዲ ያለባቸውን ሰዎች ለመመርመር ሊጠቅም ይችላል።
ሲቲ ስካኖች የሰውነትን ክፍል በደንብ ጠለቅ ያለ ምስል ለማግኘት ሙሉ ተከታታይ የራጅ ምስሎችን ይጠቀማሉ። ስካነሩ የዶናት ቅርጽ ያለው ነው፣ እና በተለያዩ ማዕዘናት ራጆች ይወሰዳሉ፣ የሚወጡት ምስሎች አንድላይ ይጣመሩና 2D (ሁለት ዳይሜንሽናል) የሰውነትን መስቀለኛ ክፍሎችን ይፈጥራሉ።
ሁልግዜ የምግብ መፍጫ ስርዓት በራጅ በደንብ አይታይም፣ ስለዚህ የበለጠ ግልጽ የሆነ ምስል ለማውጣት እንዲረዳ ባሪየም ሊሰጥዎት ይችላል። ይህ ምንም ጉዳት የሌለው ነጭ ንጥረ ነገር ወደ ሰውነት ውስጥ የማይገባ ሲሆን፣ ይልቁንም በአንጀት ውስጠኛው ክፍል ላይ ጊዜያዊ ሽፋን ይፈጥራል። ራጅ በባሪየም ውስጥ ማለፍ አይችልም, ስለዚህ ራጅ ሲነሳ የአንጀትን ግልጽ የሆኑ ምስሎችን ያሳያል። ባሪየም በሆድ፣ በትንሹ አንጀት ወይም በደንዳኔ ውስጥ ያሉ ስራዎችን ችግር እንዲያሳይ፣ ወይም በትልቁ አንጀት ውስጥ ቁስለት ካለ ለማየት እንዲረዳ በመጠጥ መልክ ሊሰጥ ይችላል።
የሆድ አልትራሳውንድ
የአልትራሳውንድ ስካነሮች ምስልን ለመፍጠር በጣም ከፍተኛ ሞገድ ያለው የድምፅ ሞገዶችን በመጠቀም ይሰራሉ። በእጅ የሚያዝ ዳሳሽ በቆዳው ላይ ይንቀሳቀሳል፣ እና ይህ የሚያስተጋባው የውስጥ አካላት ‘የሚያወጡት’ የድምፅ ሞገድ ምልክቶችን ይልካል። ከዛ ስካነሩ የሚያስተጋባውን ድምፅ ይወስድና ወደ ምስል ይቀይረዋል።
የአልትራሳውንድ ስካን የሃሞት ጠጠር እና የኩላሊት ጠጠርን ለማየት ሊያገለግል ይችላል። በተጨማሪም የተጠራቀሙ ፈሳሾች የሚገኙባቸውን እና የወፈረ እና የቆሰለ የአንጀት ግድግዳ ክፍሎችን በመለየት ረገድ ጥሩ ናቸው። አልትራሳውንድ በተጨማሪም እባጭ እና ፊስቱላስን ያሳያል። (የተለያዩ የአንጀት ክፍሎችን የሚያገናኙ ያልተለመዱ ቱቦዎች)።
ኤም አር አይ ስካን
ኤም አር አይ ስካን መስቀለኛ የሆነ የሰውነት ክፍል ምስሎችን ለማውጣት ያገለግላል። በተለይም በልጆች ላይ ራጅን መጠቀም ስለሚከለክሉ አይ ቢ ዲን ለመመርመር በከፍተኛ ደረጃ ይጠቀሙታል። በምትኩ፣ የሰውነትን የውስጥ ምስሎች ለመፍጠር ጠንካራ መግነጢሳዊ ሀይሎችን እና የሬዲዮ ሞገዶችን ይጠቀማሉ።
ኤም አር አይ ስካን መስቀለኛ የሆነ የሰውነት ክፍል ምስሎችን ለማውጣት ያገለግላል። በተለይም በልጆች ላይ ራጅን መጠቀም ስለሚከለክሉ አይ ቢ ዲን ለመመርመር በከፍተኛ ደረጃ ይጠቀሙታል። በምትኩ፣ የሰውነትን የውስጥ ምስሎች ለመፍጠር ጠንካራ መግነጢሳዊ ሀይሎችን እና የሬዲዮ ሞገዶችን ይጠቀማሉ።
የኤም አር አይ ስካነር ረጅም ቱቦ ወይም ዋሻ ይመስላል፣ እና ቀስ ብሎ ተንሸራቶ ወደዚህ ዋሻ በሚገባ በተንቀሳቃሽ ጠረጴዛ ላይ እንዲተኙ ይጠየቃሉ። ኤም አር አይ ስካን እንደ ጡንቻ እና አንጀት ያሉ ለስላሳ ህብረ ህዋሶች እንዲሁም እንደ ጉበት ያሉ የአካል ክፍሎችን ለመመልከት ጥሩ መንገድ ነው። ምክንያቱም በተለይ የፊስቱላ እና እባጭን (የተለያዩ የአንጀት ክፍሎችን የሚያገናኙ ያልተለመዱ ቱቦዎች) በመለየት እንዲሁም አዲስ እና ነባር ቁስል እና ጠባሳን በመለየት ረገድ ውጤታማ ነው።