አይ ቢ ዲ ምንድነው?

የአንጀት ቁስለት በሽታ ወይም አይ ቢ ዲ፣ ተመልሶ የሚመጣ እና የሚያገረሽ፣ የምግብ መፍጫ ስርዓትን(ይህም አንጀት ወይም የምግብ ቧንቧ ተብሎ ሊጠራ ይችላል) የሚያውክ፣ ስር ሰደድ (የረጅም ግዜ) በሽታ ነው።

በዘር, አንጀት ውስጥ በሚገኝ የባክቴሪያ አይነት እና የአንጀት በሽታን የመከላከል አቅም ባልተለመደ መልኩ መስራት ብዙ ቁጥር ካላቸው የአኗኗር ሁኔታዎች ጋር በመጣመር ይከሰታል። አይ ቢ ዲ ሁለት የሚታወቁ እና አልፎ አልፎ ተደራራቢ ይዘት ያላቸው፣ የክሮንስ በሽታ እና አልሰሬቲቭ ኮላይትስ በመባል ይታወቃሉ። አይ ቢ ዲ በማንኛውም ዕድሜ ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል, ነገር ግን በአብዛኛው የሚከሰተው በወጣትነትና በጎልማሳነት የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ ነው። አይ ቢ ዲ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን ይህም ደቡብ አፍሪካን ይጨምራል።