የ አይ ቢ ዲ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የአንጀት ቁስለት በሽታ ምልክቶች የተለያዩ ሲሆኑ የበሽታው መከሰት ደግሞ ድንገተኛ ወይም በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ ሊያድግ የሚችል ነው

ተቅማጥ

በ አይ ቢ ዲ ውስጥ ያለው ተቅማጥ እንደ ጋስትሮኢንተራይተስ (የቫይረስ ወይም የባክቴሪያ ኢንፌክሽን) ወይም አብዛኛው ሰው በተወሰነ ጊዜ ወይም በሌላ ጊዜ ከሚያጋጥመው የምግብ መመረዝ ወይም ከወፍራሙ አንጀት ብግነት የበሽታ ምልክቶች ጋር ሊከሰት ከሚችለው ተቅማጥ ከመሳሰሉት በጣም የተለመዱ ሁኔታዎች ወይም ምልክቶች ጋር ከተያያዘ ተቅማጥ የተለየ ነው። በ አይ ቢ ዲ ውስጥ ያለው ተቅማጥ በአንድ ጊዜ ለሳምንታት ወይም ለወራት የሚቆይ ሲሆን ብዙ ጊዜ መጥፎ በሆኑ ቀናት ሊያንስ ወይ ሊጨምር ይችላል። ወደ መጸዳጃ ቤት የማያስደርስ (መቋጠር የማያስችል) አጣዳፊ የሆነ ከባድ ግፊት ያለው ተቅማት ያስከትላል። ተቅማጡ ደም፣ ንፍጥ ወይም መግል ይኖረዋል። በየጊዜው ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስዎት ተቅማጥ ሌላው የ አይ ቢ ዲ ምልክት ሊሆን ይችላል።

ትኩሳት

ዝቅተኛ ደረጃ ትኩሳት የ አይ ቢ ዲ ምልክት ሊሆን ይችላል።

ሆድ ውስጥ ቁርጠት ህመሞች

እነዚህ በጣም ከባድ እና ብዙ ጊዜ ከምግብ በኋላ ወይም ከሰገራ በፊት ሊከሰቱ ይችላሉ።
ድካም
ይህ ምናልባት በሽታው በራሱ, በደም ማነስ (በደም እጥረት) ወይም በህመም ወይም በተቅማጥ ምክንያት ከእንቅልፍ መንቃት ይሆናል።

የምግብ ፍላጎት ማጣት እና ክብደት መቀነስ

የሰውነት ክብደት መቀነስ በአንጀት ውስጥ ባለው ቁስለት ምክንያት ከሚመገቡት ምግብ ውስጥ ንጥረ-ምግቦችን ወደ ውስጥ ባለመውሰዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል.

አይ ቢ ዲ ያለባቸው አንዳንድ ሰዎች፣ በተለይም ክሮንስ፣ የሚከተሉትን ጨምሮ ውስብስብ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡-

ስትሪክቸርስ

በዚህ ጊዜ እየቆሰለ ሳለ እና ከዚያም በአንጀት ውስጥ እየዳነ ሲመጣ ይህም ጠባሳ ህብረ ህዋስ ወይም ቲሹ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል. ይህ የአንጀት ክፍልን በማጥበብ አንጀት ወይም ትልቁ አንጀት ውስጥ እንዲዘጋ በማድረግ ስትሪክቸር ተብሎ የሚጠራን ነገር ሊፈጥር ይችላል።

ፊስቱላስ

እነዚህ በ ክሮንስ በሽታ የተያዙ ሰዎች ላይ በጣም የተለመዱ ናቸው። ፊስቱላ የክሮንስ በሽታ በአንጀት ወይም በትልቁ አንጀት ሽፋን ክፍል ውስጥ “ሲቦረቦር” የሚፈጠር ያልተለመደ ትቦ ወይም መተላለፊያ ነው። ፊስቱላስ ብዙውን ጊዜ በክሮንስ በሽታ በፊንጢጣ አካባቢ (የፊንጢጣ ፊስቱላ) የሚከሰት እብጠት ወይም ንፍጥ፣ መግል የሚያመነጭ ወይም ሰገራ ያለው በጣም ህመም የሚያስከትል ነው። ፊስቱላስ በቆዳ ላይ ሊወጣ (ኢንተሮክታነስ ፊስቱላ) ወይም አንዱን አንጀት ከሌላው አንጀት ጋር ሊያገናኝ ይችላል (ውስጣዊ ፊስቱላ)።

አይ ቢ ዲ አንዳንድ ጊዜ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል. እነዚህ የ አይ ቢ ዲ ከአንጀት ውጭ ያሉ ምልክቶች ይባላሉ እና በጣም የተለመዱት የሚያካትቱት:

የመገጣጠሚያዎች ህመም

የመገጣጠሚያ ሕመም አብዛኛው ግዜ አርተራይተስ ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን፣ ይህም በመገጣጠሚያ አካባቢ ፈሳሽ በማቆር ምክንያት በጣም ህመም ያለው እብጠት የሚፈጥር ነው። ብዙውን ጊዜ የእጅ እና እግር ትላልቅ መገጣጠሚያዎች ክርን፣ የእጅ እንጓ፣ ጉልበት እና ቁርጭምጭሚትን ጨምሮ ይጎዳል።

የታችኛው ወገብ ህመም

አይ ቢ ዲ ከታችኛው ወገብ እና ከዳሌ አጥንት መቆጣት ወይም ብግነት ጋር የሚዛመድ ሲሆን አንኪሎዚንግ ስፖንዳላይተስ ተብሎ ይጠራል። ይህ ሁኔታ የታችኛው ወገብ ህመም እና የወገብ ግትርነትን ያመጣል

የአይን እብጠት

የ አይ ቢ ዲ ችግር ያለባቸውን ሰዎች የሚያጠቃው በጣም የተለመደው የዓይን ሕመም ኤፒስክለራይተስ ሲሆን ይህም የአይንን ፅኑእ ልባስ የሚሸፍነውን የቲሹ ሽፋን በመጉዳት፣ የአይን ውጫዊውን ነጭ ሽፋን በማቅላት፣ በማሳመም እና በማቃጠል ይጎዳል።

የቆዳ ችግር

በርካታ የቆዳ ችግሮች ከ አይ ቢ ዲ ጋር የተቆራኙ ሲሆኑ በታችኛው እግር ክፍል ላይ ቀይ ህመም ያለው እብጠት (ኢሪቲማ ኖዶሰም) እና ህመም ያለው የቆዳ አልሰር (ፓዮደርማ ጋንግሮነሰም) የሚያካትት ከአይ ቢ ዲ ጋር የሚዛመድ በጣም የተለመደ የቆዳ ህመም ነው።