አልሰሬቲቭ ኮላይተስ ምንድነው?

አልሰሬቲቭ ኮላይትስ ትልቁ አንጀትን ብቻ የሚያጠቃ የአንጀት ቁስለት በሽታ አይነት ነው።

የላይኛውን የትልቁ አንጀት ክፍልን በማቁሰል “ኮላይተስ” ወይም የትልቁ አንጀት ቁስለትን ያስከትላል። አልሰሬቲቭ ኮላይተስ ፊንጢጣን (ፕሮክታይተስ) ወይም አጠቃላይ ትልቁ አንጀትን ብቻ ሊጎዳ ይችላል (ፓንኮላይተስ)። ተቅማጥ፣ ደም እና ንፍጥ የቀላቀለበት ሰገራ፣ እና የሆድ ቁርጠት በጣም የተለመዱ የአልሰሬቲቭ ኮላይተስ ምልክቶች ናቸው።